የኤጀንሲው መልዕክት
ውድ ተማሪዎቻችን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ከትላንት ግንቦት 17 / 2008 ዓ.ም ጀምሮ የ10ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ብሄራዊ ፈተናዎች በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ለመግለፅ ይወዳል ፡፡
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ‹‹ ፈተና ተሰርቋል ፤ መልሶቹም እነዚህ ናቸው ›› በሚል እየተለቀቁ ያሉት አፍራሽ መልእክቶች ስህተት በመሆናቸው ተማሪዎቻችን በጭራሽ እንዳትቀበሏቸው ኤጀንሲያችን በአፅንዖት እየገለፀ ፤ ዓመቱን ሙሉ በአግባቡ እየተዘጋጃችሁ የከረማችሁበትን ልፋት መና ለማስቀረት ሆን ተብሎ ማንነታቸው በማይታወቅ አካላት እየተደረገ ያለውን ሙከራ ምላሽ በመንፈግ በጋራ እንድንከላከለው ኤጀንሲያችን እያሳሰበ፤ይህንን ድርጊት በመፈጸም ላይ በሚገኙ አካላት ላይ ክትትል የጀመረ መሆኑንና በህግ የሚጠየቁበትን አግባብ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ያሳውቃል፡፡

Login Form