ወቅታዊ መረጃ

ከግንቦት 17-19/2008 ዓ/ም ለ1,064,923 ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና እንዲሁም ከሐምሌ 4-7/2008 ዓ/ም ለ253,314 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም ኤጀንሲያችን የመልስ ወረቀቶችን በመረከብ በታቀደው መሰረት ውጤቱን ለማሳወቅ በእርማት ስራው ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡
ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ የተሳሳቱ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ በርካታ ተማሪዎችና ወላጆች ውጤት ተለቋል የሚል መረጃ እንደደረሳቸውና ትክክለኛነቱን እንድናረጋግጥላቸው በተለያየ መንገድ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም እስከአሁን ከኤጀንሲያችን ውጤትን አስመልክቶ ምንም የተላለፈ መረጃ አለመኖሩን እንድታውቁ እያሳሰብን ውጤቶቹ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የሚለቀቁ ሲሆን በቀጣይ የ12 ኛም ሆነ የ10ኛ ክፍልን ትክክለኛ የውጤት መግለጫ ቀን ከኤጀንሲያችን እስከሚገለጽላችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡

Current information
The 2016 national examinations for 1,064,923 grade 10 students (EGSECE) and for 253,314 grade 12 students (EUEE) were administered form May 25-27/2016 G.C and from July 11-14/2016 G.C respectively. Consequently, the agency is engaged in correcting the collected answer sheets.
However, we are receiving different questions in relation to the exam results since different social media are announcing the result is already official. Thus, we would like to assure you there is no such information in relation to the exam result being released from the agency. Both grade 12 and 10 exam results will be released starting from half of August /2016 onward and more the agency declares that all students and parents of students to be patient and wait until it announces the exact day when the results will be official.

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail