የ12ኛ ክፍል ውጤት ተለቀቀ
በ2008 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ወይም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት መለቀቁን ኤጀንሲያችን ያሳውቃል ፡፡ ይህ ከሐምሌ 4-7 /2008 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለ 253,424 ተማሪዎች የተሰጠው የዳግም ፈተና ውጤት ሰራተኞች ባደረጉት የላቀ ርብርብና ኤጀንሲው በዚህ ዓመት በገዛቸው ተጨማሪ 10 አዳዲስ የእርማት ማሽኖች በመታገዝ በጥራትና በብቃት ታርሞ ቀደም ብሎ ኤጀንሲው በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ሊለቀቅ ችሏል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፈተና ውጤታቸውን ለማየት የሚፈልጉ ተማሪዎች በኤጀንሲው ድህረ ገፅ www.neaea.gov.et/Home/Student ገብተው በሚመጣው ሳጥን ውስጥ ሬጅስትሬሽን ቁጥራችሁን በማስገባት Go በመጫን ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም የሞባይል ስልኮቻችሁን በመጠቀም to/ለ በሚለው ቦታ 8181 በማስገባት በSMS/ በመልክት መጻፊያው ላይ rtw በማለት ስፔስ ከሰጣችሁ በኋላ የሬጅስትሬሽን ቁጥራችሁን በማስገባትና በመላክ ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail