የፈተና ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ በኤጀንሲያችንና በፖሊስ ኮሚሽነሮች መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

ትላንት በ 29/05/2008ዓ.ም ከክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የፈተና ጉዳይ ፈጻሚዎች/ተወካዮች እንዲሁም ከኤጀንሲያችን የተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ጋር ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡
በዛሬው የውይይት መርሃ-ግብር በኤጀንሲው የተዘጋጀ ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ / memorandum of understanding/ በፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ አረጋ ማማሩ እና በዳይሬክቶሬቱ የፈተና አሰጣጥ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ የበልጣል አያሌው መድረክ መሪነት ለተሳታፊዎቹ ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ረቂቅ ሰነዱ በአራት ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበ ሲሆን በተለይ በክፍል ሁለትና ሶስት ላይ በተካተተው በኤጀንሲውና በፖሊስ ኮሚሽነሮቹ በጋራ የሚከናወኑ ተግባራትን በያዙት ክፍሎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ማሻሻያዎች እንዲታከሉበት ተደርጓል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የነበሩት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተደረገው ውይይት የኔነት መንፈስ የተሞላበት ሆኖ መከናወኑን አድንቀው ለወደፊቱም እንዲሁ በተደጋጋሚ በመገናኘትና በመቀራረብ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ አገራዊ ብሎም አለም አቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ ከዚህ አንፃር የፖሊስ አካላት ትኩረት ሊሰጡት አንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም በመግባቢያ ሰነዱ ላይ በተቀመጡ ነጥቦች ዙሪያ ተሳታፊዎቹ ባነሱዋቸው ሃሳቦች መሰረት ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ የፖሊስ ኮሚሽነሮቹ ከኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ ጋር የመፈራረም ስነ-ስርዓቱ ተከናውኖ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Ifrem nanecha

Copyright © 2015-2016 National examination agency. All rights reserved.

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail