ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል?

ውድ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ (የዩኒቨርስቲ መግብያ ) ፈተና ውጤት መለቀቁ ይታወሳል፡፡ መቁረጫ ነጥቡ ተለቋል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ የሚገለጹ መረጃዎች እንዳሉና ተማሪዎችንና ወለጆችን ውዥንብር ውስጥ  እየከተቱ መሆናቸውን መገንዘብ ችለናል፡፡ መቁረጫ ነጥቡ በሚለቀቅበት ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች፤ በፌስ ቡክ ገጻች (National Educational Assessment And Examination Agency Government Organization)ና በድረ ገጻችን (www.neaea.gov.et ወይም www.nae.gov.et) የሚለቀቁ በመሆኑ በተረጋጋ ሁኔታ እንድትጠባበቁ ኤጀንሲው እየጠየቀ እስካሁን የመቁረጫ ነጥቡ ተለቋል የሚሉት መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን  እንገልጻለን፡፡

Login Form