የ2009 በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምደባ ይፋ ተደረገ
ኤጀንሲያችን የ2009 ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎች ምደባ በትላንትናው ዕለት በ12/01/09 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ በሁሉም የትምህርት መስክ የተደረገው ምደባ የተከናወነው የተማሪዎችን ውጤትና ፍላጎታቸውን መሠረት ባደረገ ውድድር መሆኑን ኤጀንሲያችን እየገለጸ፤ የተመደቡበትን ዩንቨርስቲ ለማወቅ ተማሪዎች ወደ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ በመግባት በሚመጣው ሳጥን ውስጥ ሬጅስትሬሽን ቁጥራችሁን በማስገባትና Go በመጫን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በሌላ በኩል በምዝገባ ፎርም ላይ ዜግነት ኢትዮጲያዊ ያልሆነ /none Ethiopian/ በማለት የሞሉ ተማሪዎችን ኤጀንሲያችን በምደባ ውስጥ እንዳላካተታቸው እየገለጸ ምደባውን ለማግኘ ኢትዮጵየዊነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ኤጀንሲው ድረስ በአካል በመገኘት ማመልከት እንደሚጠበቅባቸው ይገልጻል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኤጀንሲው በምንም አይነት ምክንያት ከዩንቨርስቲ ዩንቨርስቲ ቅይይር ጥያቄን እንደማያስተናግድ ያሳውቃል፡፡

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail