የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (10ኛ ክፍል) እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (12ኛ ክፍል) ፈተናዎች ምዝገባ የተላለፈ ማስታወቂያ፣

የምዝገባ ቀን፡-

ከጥር 1 – 12 ቀን 2009 ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያ በመደበኛ የሥራ ቀንና ሰዓት፡፡

የምዝገባ ቦታ፡-

የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (10ኛ ክፍል) እና የመሰናዶ (12ኛ ክፍል) መደበኛና የማታ ተማሪዎች የሚመዘገቡት በ2009 ዓ.ም በመማር ላይ ባሉበት ትምህርት ቤት ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የግል አመልካቾች እና በርቀት ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኘው የወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙት ግን በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ትም/ቤቶች ባሉባቸው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ወይም ጽ/ቤቱ በሚያዘጋጀው ምዝገባ ጣቢያ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- 

ስለ ክፍያና የምዝገባ አፈፃፀም ዝርዝር መመሪያ ታህሣሥ 30 እና ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም በሚታተመው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በየምዝገባ ጣቢያ ማስታወቂያ ሠሌዳ ስለሚገለጽ ተመዝጋቢዎች እንዲከታተሉ ኤጀንሲው ያሳስባል፡፡

በተጨማሪ የኤጀንሲውን ዌብሳይት  www.neaea.gov.et   ይጐብኙ፡
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ


Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail