የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (10ኛ ክፍል) እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የምዝገባ አፈፃፀም

የሚያበቁሁኔታዎች

የኢትዮጵያአጠቃላይ 2ደረጃትምህርትማጠናቀቂያፈተና (10ክፍል) ለመመዝገብ፣

መደበኛተማሪዎች
የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የተዛወሩና በትምህርት ሚኒስቴር ወይም በክልል ትምህርት ቢሮ ዕውቅና በተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት 9ኛ እና 10ኛ ክፍልን በሦስት ዓመት ተምረው ለማጠናቀቅ በ2009 ዓ.ም በማታ ፕሮግራም የ10ኛ ክፍል ትምህርት የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ማቅረብ የሚችሉና በመማር ላይ የሚገኙ፣

የግል አመልካቾች

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ወይም በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና (ESLCE) በመደበኛ ወይም በማታ ወይም በግል የተፈተኑበትን ሠርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ 

የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ለመውሰድ የሚያመለክቱ ተመዝጋቢዎች በተፈተኑበት ዓመት ለመሰናዶ የተቆረጠውን የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ መሆን አለባቸው፡፡

የርቀት ትምህርት ተከታትለው የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (10ኛ ክፍል) ፈተና በግል ለመውሰድ የሚፈልጉ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የተዛወሩና ዕውቅና ከተሰጠው የርቀት ትምህርት ተቋም የ9ኛ ሦስት ሴሚስተር እና የ10ኛ አንድ ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ (ትራንስክሪፕት) እና የድጋፍ ደብዳቤ ከ8ኛ ክፍል ሠርቲፊኬት ጋር በአካባቢው ለሚገኘው የወረዳ ምዝገባ ጣቢያ በማቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመመዝገብ፣

መደበኛተማሪዎች

የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት (EGSECE) ፈተና ተፈትነው በወቅቱ የነበረውን የማለፊያ ነጥብ በማምጣት የ11ኛ ክፍል ትምህርት አጠናቀው በ2009 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል በመማር ላይ ያሉ ሲሆን ዓመቶቹ ተከታታይ መሆን አለባቸው፡፡

ለማታ የመሰናዶ ተማሪዎች

የማታ ክፍለ ጊዜ የመሰናዶ መርሃ ግብር ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመቀበል የሚያመለክቱ ተመዝጋቢዎች የ10ኛን ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (EGSECE) በመቀበል ለመሰናዶ መርሐ ግብር የሚያበቃ ውጤት በማምጣት የ11ኛ እና 12ኛ ክፍልን በሦስት ዓመት ተምረው ለማጠናቀቅ በ2009 ዓ.ም በማታ ፕሮግራም በመከታተል ላይ ያሉ፣ ለዚህም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሠርቲፊኬት፣ የ11ኛ ክፍል ያጠናቀቁበትን እና የ12ኛ ክፍል የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ማቅረብ የሚችሉ፣

ለግል የመሰናዶ ተማሪዎች

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በግል ፈተናውን ለመውሰድ የሚያመለክቱ ተመዝጋቢዎች በተፈተኑበት ዓመት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ማለፊያ ነጥብ ያላመጡና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያልተደለደሉ ብቻ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሠርቲፊኬት በማቅረብ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡

2.  የመመዝገቢያ ቦታ

የ10ኛ ክፍል እና የመሰናዶ (12ኛ ክፍል) መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች የሚመዘገቡት በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመማር ላይ ባሉበት ትምህርት ቤት ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የግል አመልካቾች ምዝገባ የሚካሄደው በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኘው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሲሆን የአዲስ አበባ የግል አመልካቾች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ወይም ጽ/ቤቱ በሚያዘጋጀው ምዝገባ ጣቢያ ይሆናል፡፡

3.የመመዝገቢያ ጊዜ

የስም ለውጥ ለማድረግ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች ከምዝገባ በፊት ስማቸውን በሕግ አስቀይረው የተፈቀደበትን የፍርድ ቤት ማስረጃ በምዝገባ ወቅት በማቅረብ ምዝገባቸውን በአዲሱ ስም መፈጸም ይችላሉ፡፡ ምዝገባ ከተፈጸመ በኋላ የሚቀርቡ ማናቸውም ዓይነት የስም ለውጥ ጥያቄዎች ኤጀንሲው አያስተናግድም፡፡

ግዕዝ፣ ፈረንሣይኛ፣ እና ሌሎች የብሔር ብሔረሰብ ቋንቋዎች ፈተናዎችን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ፈተና በመደበኛነት ለመፈተን የሚያመለክቱ ሁሉ ትምህርቱን እንዲያስተምሩ ዕውቅና ከተሰጣቸው ት/ቤቶችና ክልሎች በመደበኛ ትምህርት ቤት በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ቋንቋውን ለመማራቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ግዕዝ፣ ፈረንሣይኛ፣ እና ሌሎች የብሔር ብሔረሰብ ቋንቋዎችን በግል ለመመዝገብ የሚችሉት ቋንቋውን እንዲያስተምሩ ዕውቅና በተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል አጠናቀው የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ኦሪጅናል ትራንስክሪፕትና በነዚህ ቋንቋዎች ውጤት የተመዘገበበትን ሠርቲፊኬት ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡

የግል አመልካቾች በግንባር ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻቸው አማካኝነት ለመመዝገቢያ ለየትምህርት ዓይነቱ የሚደረገውን ክፍያና አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃዎች አሟልተው በማቅረብ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡

ከምዝገባ መመሪያ ውጪ የተፈጸመ ምዝገባ በማንኛውም ወቅት ሲታወቅ የሚሰረዝ ሲሆን፣ ለአገልግሎት የተከፈለው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም፡፡ ስለዝርዝር የምዝገባ አፈፃፀም እና የምዝገባ ፎርም አሞላል ምዝገባ ጣቢያዎች በመሄድ መረዳት ይቻላል፡፡

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

የስልክ ቁጥር011-1-232874

011-1-232889

011-1-232878

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail