የ2008 ዓ/ም የፈተና አሰጣጥ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 5/2008 ዓ/ም በኤጀንሲያችን በሚገኘው ኮንፈረንስ ክፍል ጥሪ የተደረገላቸው የኢቢቪ፣ ኢዜአ፣ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ ኦሮሚያ ቲቪ፣ አዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ሚዲያዎች በተገኙበት የኤጀንሲያችን ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሄር የ2008 ዓ/ም የፈተና ዝግጅት፣ ስርጭትና፣ አሰጣጥ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫውም አጠቃላይ የፈተና ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እንደተጠናቀቀና፣ የፈተና ስርጭት ቅድመ ዝግጅቱም በተሳለጠ መልኩ እየደሄደ እንደሚገኝ ብሎም ከተደረገው አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅት አንጻር የፈተና አሰጣጡም በተሳካ ሁኔታ እንደሚጠናቀቅ ሙሉ እምነታቸው መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
ከዘህም ጋር አያይዘው የፈተና ደንብ ጥሰቱን ለመከላከል በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰራ አሳስበዋል፡፡
ከመግለጫው በመነሳት በኮንፈረንሱ ተካፋይ የነበሩት ጋዜጠኞች ፈተናው ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር አስገዳጅ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸውን፣ ፎርም ከሞሉ በኋላ በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ ተማሪዎች የፈተና ደንብ ጥሰቱን ከማባባስ አኳያ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አንጻር ኤጀንሲው ምን እየሰራ እንደሚገኝ ብሎም የፈተና ደንብ ጥሰቱን ለመከላከል ከኅብረተሰቡ ምን ይጠበቃል የሚሉ ዋና ዋና ጥያቄዎችና የመሳሰሉት ቀርበው ነበር፡፡ አቶ አርአያም ሲመልሱ እስካሁን ባለው ሁኔታ በቅርቡ በኦሮምያ ተከስቶ ከነበረው ችግር አኳያ በ23 ት/ቤቶች የ10ኛ ክፍል እንዲሁም በ12 ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናዎች ወደሌላ ጊዜ የተዘዋወሩበት ሁኔታ እንዳለና ከዛ ውጪ ፈተናው በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡ ፎርም ከሞሉ በኋላ ወደ ት/ቤት በማይገኙ ተማሪዎች ዙሪያ ለተነሳው ጥያቄ ት/ቤቶች ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ በመረጃ በተደገፈ ሁኔታ ለኤጅንሲው ሲያቀርቡ ተማሪዎቹ ለፈተና እንዳይቀመጡ የሚታገዱበት ሁኔታ እንዳለ አስገንዝበው የፈተና ደንብ ጥሰትን አስመልክቶ ኅብረተሰቡ ልጆቹን በስነምግባር ከማነጽ ጀምሮ ሙሉ ድጋፉን በጸረ ኩረጃ አስተሳሰብ ላይ በማድረግና ሙሉ ድጋፉን በመስጠት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፈተና ስነ ምግባር ጥሰትን በማስወገድ ህዳሴያችንን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል በፖሊስ ማርሽ የታጀበ ደማቅ መርሃ ግብር በኤጀንሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከናውኗል፡፡ መርሃ ግብሩ መላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ተካፋይ የሆኑበት ነበር፡፡

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail