‹‹የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰትን በማስወገድ ህዳሴያችንን እናረጋግጥ ›› በሚል ርዕስ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ . ም የምክክር ጉባኤ አካሄደ ፡፡
በዚህ የምክክር ጉባኤ ላይ የኤጀንሲው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራንና ወላጆች ተገኝተዋል ፡፡ የምክክር ጉባኤውን በመምራትና በማወያየት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኞችም ሚና እንደነበራቸው ለማወቅ ተችሏል ፡፡አቶ አሸናፊ ጅማ የፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ማኔጂንግ ዳይሬክተር እንግዶቹን እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የእለቱ የክብር እንግዳ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል ፡የእለቱን የምክክር ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክትር አቶ አርዓያ ገ/እግዚአብሔር ናቸው ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው የትምህርት ጥራት ነቀርሳ የሆነውን ኩረጃን ለመከላከል እዚህ የተገኘን ባለድርሻ አካላት በሙሉ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለብን በመሆኑ መፍትሄ ላ|ይ የተኮረ ምክክር እንደምናደርግ እምነቴ ነው ብለዋል ፡፡ አያይዘውም የዛሬው የምክክር ጉባኤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዳይቻል በከፍተኛ ደረጃ እንቅፋት እየሆነ ያለውን ኩረጃን ለማስወገድ ኤጀንሲው ከባለፉት አራት አመታት ጀምሮ እየሰራቸው ካሉት ስራዎች መካከል አንደኛው እንደሆነ ገልፀዋል በሌላ በኩልም የከፍተኛ ትምህርት ምደባን አስመልክቶ በቀረበው የባለሙያዎች ፅሁፍ ላይ እንደተካተተው በዩንቨርሲቲዎች ምደባ ወቅት በተደጋጋሚ ኤጀንሲውን የሚያጋጥሙት ችግሮች ተብራርተዋል ፡ ፡ በተለይም ከምደባ ጋር ተያይዞ አወንታዊ ድጋፍ ፈላጊ ተማሪዎች ምደባ ከመውጣቱ 15 ቀናት ቀደም ብሎ ማስረጃቸውን ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ ጋር አያይዘው ለኤጀንሲው እስካላቀረቡ ድረስ አጀንሲው ምደባዎችን ይፋ ካደረገ በኋላ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለመቀበል እንደሚቸገር ባለሙያዎቹ አብራርተው የእለቱ የምክክር ጉባኤ ተጠናቋል ፡፡

Login Form

Notifications

የኢትዮጵያ የ2009 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ detail
የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 2009ዓ.ም UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION TIME TABLE 2017 detail
የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ሰሌዳ 2009 ዓ.ም G -10 EGSECE TIME TABLE 2017 detail
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የተማሪዎች ጥያቄ ????? detail
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ detail
ማሳሰብያ ፡ መቁረጫ ነጥብ ተለቋል? detail
የኤጀንሲው መልዕክት detail